አካስ ኢንጂነሪንግ

AKASS Engineering

Your ICT Partner in Ethiopia

ሰለ አካስ ኢንጂነሪንግ

አካስ ኢንጂነሪንግ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት ሠጪ፣ የቴክኖሎጂ እቃዎች አቅራቢና አማካሪ ድርጅት ነው። ድርጅቱ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 2015  ዓ.ም. ከተልያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በምህንድስና እና ልዩ ልዩ ዘርፎች በአንደኛና ሁለተኛ ዲግሪ ተመርቀው በመስኩ ለበርካታ አመታትን ባገለገሉና ከመደበኛው ትምህርት በተጨማሪ በርካታ ምስክር ወረቀቶችን ( from Cisco, CompTIA and GVF (VSAT), Microsoft, software development) በያዙ መኃንዲሶች የተመሰረተ ተቋም ነው።

መሐንዲሶቻችን በአገርወስጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃዎች በመዘዋወር በርካታ ሥራዎችን ያከናወኑ ሲሆን፣ በሃገርውስጥ ከሰሜን እስከደቡብ፤ ከምስራቅ እስከ መራብ እጅግ ገጠራማ የሆኑ አካባቢዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ለመትከልና ለመጠገን የተዘዋወሩ ሲሆን፤ በዐለም አቀፍ ደረጃ ከአውሮፓ በበርካታ አገሮች፣ በሰሜን አሜሪካ በርካታ ግዛቶች፣ በአፍሪካ በርካታ አገሮች እንዲሁም በመካከልኛው ምስራቅ አገራት በመዘዋወር ያገለገሉና በርካታ ስልጠናዎችን በመውሰድ ልምድን ያካበቱ ናቸው።

ይህንድ ድርጅት ልማቋቋም የተነሳሱበት ዋና አላማም፣ ያካበቱትን ልምድ በመጠቀም፣ በተለይመ በሃገራችን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለውን የአገልግሎት ክፍተት ወደላቀ ደረጃ ለማሻገር የበኩላቸውን አስተዋጾ ለማድረግ በማሰብ ነው።