- ሃንዳይ በየጊዜዉ አዳዲስ ሞዴሎችን የሚያወጣ ሲሆን ሰፊ አማራጭ ሞዴሎችም ሲያመርት ከላይ የተጠቀሱትን በማሟላት አህጉር/አገር ተኮር በሆነ መልኩ ነው፤
- ሃንዳይ ዓለም ላይ ካሉት የተሸከርካሪ ብራንዶች በከፍተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ፕሪሚየር ብራንድ ደረጃን የያዘ ነዉ፡፡ ይሄዉም በሚያመርታቸዉ በሁሉም ሞዴሎች ነው፤
- ፕሪሚየም ብራንድ ተጨማሪ ክፍያ ያለዉ ቢሆንም ኩባንያችን ያለተጨማሪ ክፍያ ተሸከርካሪዎቹን ማቅረቡ ፤
- አንድ አዉቶሞቲቭ ኩባንያ የተሟላ ነዉ የሚባለው ቢያንስ ሶስቱን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሽያጭ አገልግሎቶች እና ዋስትና ሲያሟላ ነዉ፡-
- የተሸከርካሪ ሽያጭ
- የኦርጅናል መለዋወጫ ሽያጭ
- የጥገና አገልግሎት
- የአምራች ኩባንያ ዋስትና
- ዋስትና፡-
ዋስትና ማለት በአምራች ኩባንያዉ የምርት ሂደት እና የማቴሪያል ጥራት ጉድለት ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮችን በማስተካክል ወይም በመቀየር ወደነበረበት ሁኔታ መመለስ ነዉ፡፡ ይሄዉም በአምራች ኩባንያዉ ህጋዊ ወኪል ሲረጋገጥ ነዉ፡፡ (ለበለጠ መረጃ የዋስትና ደብተርዎን ይመልከቱ)
- የዋስትና ጊዜ የሚሸፍነዉ ተሸከርካሪውን ከተረከቡ ቀን ጀምሮ 3 ዓመት ወይም 60,000 ኪ.ሜ ሲሆን ከሁለት አንዱ ቀድሞ ሲደርስ ያበቃል፤
- ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ዋናው ባትሪ ዋስትና 8 ዓመት ወይም 160,000 ኪ.ሜ ሲሆን ከሁለት አንዱ ቀድሞ ሲደርስ ያበቃል፤
- ዋስትና የሚሰጠዉ ሃንዳይ ሞተር ኩባንያ (አምራቹ) በህጋዊ ወኪሉ በኩል ብቻ ሲሆን ሌላ ማንም መስጠት አይችልም ምክንያቱም ዋስትና አህጉር/አገር ተኮር ከመሆኑም በተጨማሪ ህጋዊ መስመር ተከትሎ የሚሰጥ በመሆኑ ነዉ፤
- ኩባንያችን የሸጣቸዉን ተሽከርካሪዎች በሚያስረክብበት ጊዜ የዋስትና ደብተር ይሰጣል ይሄም ማረጋገጫዎ ነዉ፤
- የዋስትና ተጠቃሚ ለመሆን የተሽከርካሪዉ አጠቃቀም ደብተር (Owner`s manual ) ላይ በተቀመጠዉ መሰረት በሃንዳይ ሞተር ኩባንያ ህጋዊ ወኪል የጥገና ማዕከላት ተሸከርካሪዉ ሰርቪስ መደረግ አለበት፤
- በህጋዊ ወኪሉ በኩል ለሽያጭ ያልቀረበ ተሸከርካሪ ዋስትና ስለማይኖረዉ ላልታሰበ ከፍተኛ ወጪ ይዳርጋል፤
-
አስተማማኝ የድህረ-ሽያጭ አገልግሎት
- ከክፍያ ነፃ የመጀመሪያ 1,000 ኪ.ሜ ፍተሻ
- ከክፍያ ነፃ የእጅ ዋጋ ለመጀመሪያዉ 5,000 ኪ.ሜ ሰርቪስ
- የኦሪጂናል መለዋወጫ ዕቃዎች አቅርቦት በቀጥታ ከእናት ኩባንያችን ከሃንዳይ ሞተር ኩባንያ በማስመጣት
- ተሽከርካሪ ከአምራች ኩባንያዉ ህጋዊ ወኪል ሲገዙ የኦርጅናል መለዋወጫ ዕቃ እና የጥገና አገልግሎት ማግኘትዎን እርግጠኛ ይሆናሉ፡፡ ይሄንንም በመጎብኘት ማረጋገጥ ይችላሉ$
- ለተሸከርካሪዎ ኦሪጂናል መለዋወጫ ዕቃ መገጠሙን ለማረጋገጥ የተቀየረውን መለዋወጫ ይረከባሉ፤
- ለተሽከርካሪዎ ኦሪጅናል መለዋወጫ ዕቃ በመገጠሙ ከፍተኛ መዋዕለንዋይ ያወጡበት ተሽከርካሪዎ ጤናማ " ከብልሽት የተጠበቀ " ተጨማሪ ወጪ የማያስወጣዎት ስለሚሆን ተሽከርካሪዎን እርግጠኛና ደስተኛ ሆነው በሙሉ ልብ ያሽከረክራሉ፤
- አያድርስና ተሽከርካሪዎ ኩባንያችን ለጥገና ገብቶ በሚቆይበት ጊዜ አደጋ ቢያጋጥመዉ ሙሉ የመድህን ዋስትና ሽፋን ስላለው ስጋት አይገባዎትም፤
- ተሽከርካሪዎ ወደ ጥገና ማዕከላችን ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ጥገናዉ ተጠናቆ እስኪረከቡ ድረስ ለየት ያለ ጥንቃቄ ደረግለታል፤
- ተሽከርካሪዎ የሚያስፈልገውን ወቅታዊ ጥገና (Periodical Service) በተከታታይ በጥገና ማዕከላችን የሚያስጠግኑ ከሆነ የተሽከርካሪዎ የጥገና ታሪክ (Periodical service history) በመረጃ gታችን ውስጥ ተመዛግቦ ስለሚገኝ ተሸከርካሪዎን መቀየር/መሸጥ በሚፈልጉበት ወቅት የተሽከርካሪዎን የጥገና ታሪክ የሚገልጽ የምስክር ወረቀት እና ነፃ የፍተሻ አገልግሎት ያገኛሉ፡፡ ይህም መኪናዎን በሚጠብቁት ዋጋ ለመሸጥ ይረዳዎታል (Resale value ይጨምራል)፤
- እንደ የጥገና አይነቱ ከጎን በተዘረዘሩት እጅግ ዘመናዊ የጥገና መሳሪዎች በመታገዝ በሰለጠኑና ብቃት ባላቸው ባለሞያዎች ተሽከርካሪዎ ሰርቪስ መደረጉ ሁሌም ሲያሽከረክሩ በሙሉልብና ከስጋት ነፃ በሆነ ሁኔታ ይሆናል፤
- ከኩባንያችን ተሸከርካሪ ለመግዛት የባለሙያ ምክር ሲያስፈልግዎ የሽያጭ አማካሪዎቻችን እርስዎን ለማገልገል ዝግጁ ናቸዉ
- ኩባንያችን ስለሚሰጠዉ የተሸከርካሪ ጥገና እና ስለ ኦርጅናል መለዋወጫ ዕቃዎች ምክር ሲፈልጉ የጥገና አማካሪዋቻችን እና የመለዋወጫ ሽያጭ ባልደረቦችን እገዛ ማግኘት ይችላሉ
- ኩባንያችን ሁሌ አዳዲስ ሀሳቦችን እና አሰራሮችን ይተገብራል፡፡ አንድ ሀሳብ ፍፁም ብቸኛ የመፍትሄ አካል ነዉ ብሎ አያምንም
- አገልግሎታችንን በሚያገኙበት ወቅት ማለትም የተሸከርካሪ ሽያጭ " የመለዋወጫ ዕቃዎች ሽያጭ እና የጥገና አገልግሎትን አስመልክቶ ማንኛውንም ቅሬታም ሆነ አስተያየት በየደረጃው ላሉ የስራ ኃላፊዎች በማሳወቅ መፍትሄ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ይሄንንም ኩባንያችን ያበረታታል፡፡
- ኩባንያችን የዉድ ደንበኞቻችንን ፍላጎት ለመስማት" ለመቀበል" በተቻለ መጠን ፍላጎትዎን ለማJላት ፍፁም ፍቃደኛ እና አጋዥ ለመሆን ዝግጁ ነዉ፡፡ በቃል ከሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ በተጨማሪም ዉድ ጊዜዎን ሰዉተዉ በፅሁፍ ለሚሰጡን ሃሳቦች በኩባንያችን ዋና ስራ አስፈፃሚ ብቻ የሚታዩ የሃሳብ መስጫ ሳጥኖቻችንን እንዲጠቀሙ እንጋብዛለን
- የሃንዳይ-ማራቶን ሞተር ቤተሰብ በመሆንዎ ሁሌም ምስጋናችን ከልብ ነዉ፡፡ እርስዎን ይበልጥ ለማገልገል አበክረን እንሰራለን
ስለጎበኙን እናመሰግናለን!!
መልካሙ አሰፋ
መስራች ዋና ስራ አስፈፃሚ እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር
አስተያየት ለመስጠት፡
-
-
-
- ድህረ ሽያጭን (የመለዋወጫ ሽያጭ እና የጥገና አገልግሎት) በተመለከተ፡ የድህረ ሽያጭ ዳይሬክተር ስልክ ቁጥር +251-929-906255
- የተሸከርካሪ ሽያጭን በተመለከተ፡ የመገጣጠሚያ እና ሽያጭ ሲኒየር ዳይሬክተር ስልክ ቁጥር +251-911-522762
- ኢ-ሜይል፡
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
-
-